Wednesday, May 9, 2012

ወልዶ መሣም

የአብራኬ ክፋይ ፣የቅስሜ
የእኔነቴ ውርስ፣የደሜ
በምድር፣የብቻ ትርጉሜ
ማግኘት፣እንዲህ ይጥማልና፣ለስሜ
     የመልኬን ቅጂ ጥላ መሣይ
     ሁለመናዬ ሠርፆበት ሲታይ
     ገፄ በፀዳሉ ላይ
     ምስሉ ስለ እኔ ሲያወያይ
     ለካ ወልዶ ላየ ነው ዕርካታው፡፡
ማማ፣ ባባ ሲል በኮልታፋው
በእምቦቀቅላ አፉ ሚናኘው
ድክድክ ሲል ባልጠነከረው
በህፃን ገላ ጨቅላው
የጠረኑ ለዛ መዓዛው
ለካ እንዲህ ነበርና ሚያውደው ፡፡
     ወልዶ የመሣም ፍችው
     አውቆ ላጣጣመ ቃናው
     የፍስሀ ትሩፋት ፀጋው
     በመሐፀን ሣለ ለባረከው
በእግዜር ፊት ስለውሎው
የሚያሣርጉ መላዕክታት ያለውwww.facebook.com/tarikuasefa
ህፃን ፣ ወልዶ መሣም ጣዕምናው
ለካ :እንዲህ ነበርና ደስታው
ለወላጅ :የውስጥ እርካታ እሚሠጠው፡፡
የአብራኬ ክፋይ ፣የቅስሜ
የእኔነቴ ውርስ፣የደሜ
በምድር፣የብቻ ትርጉሜ
ማግኘት፣እንዲህ ይጥማልና፣ለስሜ
     የመልኬን ቅጂ ጥላ መሣይ
     ሁለመናዬ ሠርፆበት ሲታይ
     ገፄ በፀዳሉ ላይ
     ምስሉ ስለ እኔ ሲያወያይ
     ለካ ወልዶ ላየ ነው ዕርካታው፡፡
ማማ፣ ባባ ሲል በኮልታፋው
በእምቦቀቅላ አፉ ሚናኘው
ድክድክ ሲል ባልጠነከረው
በህፃን ገላ ጨቅላው
የጠረኑ ለዛ መዓዛው
ለካ እንዲህ ነበርና ሚያውደው ፡፡
     ወልዶ የመሣም ፍችው
     አውቆ ላጣጣመ ቃናው
     የፍስሀ ትሩፋት ፀጋው
     በመሐፀን ሣለ ለባረከው
በእግዜር ፊት ስለውሎው
የሚያሣርጉ መላዕክታት ያለው
ህፃን ፣ ወልዶ መሣም ጣዕምናው
ለካ :እንዲህ ነበርና ደስታው
ለወላጅ :የውስጥ እርካታ እሚሠጠው፡፡

አፈወርቅ ተክሌ

Hon. Maître Artiste World Laureate Afewerk እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

ብርድ ነው ይድናል ብሎ እየተባለ
አፈወርቅ ሞተ እንዲሁ እንደሳለ።


የስዕል ፈጣሪ መሆኑን ሳያውቁ
ለስዕል እንዲሰግድ አስተማሩት ሊቁ።

ጥበብን ሁሉም ሰው  ሳይታክት ይሻታል
ነገር ግን አፈወርቅ ሽቶ አግኝቷታል።

”የትም ተወለድ አንኮበር እደግ”
ሲባል የኖረውን ልማድና ወግ
አፈወርቅ ለመሻር ፈልጎና ወድዶ
በዓለም አደገ አንኮበር ተወልዶ።

በዚያ በትርምስ፤ መላው በጠፋበት፤ በዘመነ አብዮት
ጕስቋላ ኢትዮጵያን፤ አልሳልክም እያሉ፤ አጕል ሲበቅቱት
አሽሞንሙኖ ስሏት፤ ዕድሜውን ፈጽሟል፤ ባሻቸው ይሳሏት።

ጥበብ እርሟን ታውጣ፤ መርዶውን ንገሯት፤ ከነእርሟ አትብላ
አንኮበርም ትስማ፤ ውሎ ትዋልለት፤ ገልብጣ  በርኖሷን፤ ዘቅዝቃ ነጠላ
አፈወርቅ ተክሌ፤ ዝነኛው ሠዓሊ፤ ተመልሶ አይመጣም፤ ከእንግዲህ በኋላ።www.facebook.com/tarikuasefa