Wednesday, May 9, 2012

አፈወርቅ ተክሌ

Hon. Maître Artiste World Laureate Afewerk እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

ብርድ ነው ይድናል ብሎ እየተባለ
አፈወርቅ ሞተ እንዲሁ እንደሳለ።


የስዕል ፈጣሪ መሆኑን ሳያውቁ
ለስዕል እንዲሰግድ አስተማሩት ሊቁ።

ጥበብን ሁሉም ሰው  ሳይታክት ይሻታል
ነገር ግን አፈወርቅ ሽቶ አግኝቷታል።

”የትም ተወለድ አንኮበር እደግ”
ሲባል የኖረውን ልማድና ወግ
አፈወርቅ ለመሻር ፈልጎና ወድዶ
በዓለም አደገ አንኮበር ተወልዶ።

በዚያ በትርምስ፤ መላው በጠፋበት፤ በዘመነ አብዮት
ጕስቋላ ኢትዮጵያን፤ አልሳልክም እያሉ፤ አጕል ሲበቅቱት
አሽሞንሙኖ ስሏት፤ ዕድሜውን ፈጽሟል፤ ባሻቸው ይሳሏት።

ጥበብ እርሟን ታውጣ፤ መርዶውን ንገሯት፤ ከነእርሟ አትብላ
አንኮበርም ትስማ፤ ውሎ ትዋልለት፤ ገልብጣ  በርኖሷን፤ ዘቅዝቃ ነጠላ
አፈወርቅ ተክሌ፤ ዝነኛው ሠዓሊ፤ ተመልሶ አይመጣም፤ ከእንግዲህ በኋላ።www.facebook.com/tarikuasefa

No comments:

Post a Comment