Thursday, May 10, 2012

መራር ስነግጥሞች

www.facebook.com/tarikuasefawww.facebook.com/tarikuasefa

ባልን ቢያስተያዩት - ከሚስ ጋራ፣
እሷ አፍለኛ ሆነች - ! ሻጋታ እንጀራ፣ 
(መንግስቱ ለማ)

* * *
ይህ የናንተ ዘመን፣
ለካስ ከስሮ ኖሯል- የዘመን መናኛ፣
ያጠናፈረው ነው - የመታውመጋኛ፣
የደገመው ዳፍንት፣
ከፍ ብሎ አጋሰስ- ዝቅ ብሎጌኛ፣
(ዮሃንስ አድማሱ)
* * *
ዝናቡ ዘነበ  - ደጁ ረሰረሰ፣
ቤት ያላችሁ ግቡ  - የኛማ ፈረሰ፣ 
(የአማራ አርሶአደሮች) 

* * *
አባቶቻችን ምን አሉ?
እናቶቻችን ምን አሉ?
እረ ምንኛውን - ከቶ ምን ይላሉ?
ሁሉም ተሰብስበው - ጭቃ ያቦካሉ፣
ብቻ ማለቁ ነው - ውሃቸው ሁሉ፣ 
(ዮሃንስ አድማሱ) 
* * *
እናንት ቡችላዎችእንደምን አላችሁ?
እኔን ተከተሉኝ - አንድ ላይ ሆናችሁ፣
እሰጣችሁዋለሁኬክ ለያንዳንዳችሁ፣
እናንት ደደቦች!
አእምሮ ግን መስጠትአልችልም ይግባችሁ! 
(አሌክሳንድር ፑሽኪን) 
* * *
በክርስቶስ ፈንታ - ፈልጉ ክርታስ፣
የምንለጥፍበት  - የጊዜውን ነፍስ፣
በስላሴ ፈንታ - ፈልጉ ሰሌዳ፣
የምንደጉስበት - የጊዜውን ፍዳ፣ 
(ዮሃንስ አድማሱ)
* * *
አይንን ካበባ - ጆሮን ከሙዚቃ፣
ጣትን ከፒያኖ - ብራናን ከመቃ፣
ብእርን ከወረቀት - ብሩሽን ከሸራ፣
ምን ደግመው ቢጥሉ - መሆን ቢከጅሉ፣
ሞዛርትና ሳልዬር - ማለት ለየቅሉ፣
(አበራ ለማ) 
* * * 
ይማጅ ኒኸሻና፣
ይማጅ ኒቄና፣
ይማጅ ዩቅ አለው፣
ይማጅ ፈረዴይ፣ 
(ትርጉም)
የተሻለውን እንፈልጋለን፣
የተሻለውን ግን አናውቅም፣
የተሻለውን የምታውቅ ፈጣሪ ሆይ፣
የተሻለውን አምጣልን፣ 
( የሃረሪ ህዝብ) 
* * *
እኛ የሳልነው ጥርስ ካልጠረሰ በኛ፣
ለኛ ዘሮች ጦስ ነው - የሕይወት መጋኛ፣
ስለዚህ ሰዎቼ - እኔ እምቧ አልኳቸው፣
ምናልባት አጥንቴ - መረቅ ቢሆናቸው። 
(ዳኛቸው ወርቁ)
* * *
በዚህ ሙት ሕዝብ፣ በድክመቱ ብትልቁ፥ በፈተናው ብትበልጡ፣
በብሶቱ ብትፈይዱ፣
በመክሊቱ ብትነግዱ
ይህ ፍጹም ባድማ፣ ይህ ፍጹም ድቅድቅ ጨለማ
እሚበራ እንዳይመስላችሁ፣ በናንት የይስሙላ ቁራጭ ሻማ። 
(ደበበ ሰይፉ) 
* * *
ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!
ካልተጠነቀቅህ ካልበረታህ - ትሞታለህ፤
ኢትዮጵያ ሰውን ትከዳለች!
(የአድአ በርጋ ኦሮሞ) 
* * *
ተማምለን ነበር - በጋራ ልናርስ፣
ቃልኪዳን ነበረን - በጋራ ልናፍስ፣
ማተብ የሌለው ሰው - ሆዱን የሚወድ፣
ዘሬን ሸጦ በልቶ - አደረገኝ ጉድ፣
(ቅኔ - አንዳርጋቸው ፅጌ )

No comments:

Post a Comment