Friday, May 11, 2012

Gondar and its Castles/የጎንደር ከተማ ዋነኛ የቱሪስት መስህብ

www.facebook.com/tarikuasefaየጎንደር ነገስታት ግብረ ህንጻዎች በአማራ ክልል ከአዲስ አበባ ሰሜን ምዕራብ 738 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ከተማ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው አጋማሽ በአጼ ፋሲለደስ ዘመን መንግስት እንደተቆረቆረች የሚነገርላት ጎንደር ከሌሎች ቀደምት ከተሞች ለየት የሚያደርጋት ለረጅም ጊዜ በመናገሻ ከተማነት ማገልገሏ ነው፡፡ በታሪክና በባሀል ነጸብራቅነቷም ትታወቃለች፡፡ የጎንደር ከተማ ዋነኛ የቱሪስት መስህብ ሃብቶች የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ነገስታት ያሰሯቸው አብያተ መንግስትና አብያተ ክርስቲያን ናቸው፡፡ አብያተ መንግስቱ በከተማ መሃል በሚገኘው ከፍተኛ ስፍራ ላይ ከአጼ ፋሲል ግቢ ቀደም ሲል 12 በሮች እንደነበሩት ይነገራል፡፡ አሁን ያለው የመግቢያ በር ከጥንቶቹ በሮች አንዱ ሳይሆን በጣሊያን ጊዜ የተሰራ ነው፡፡ አብያተ መንግስቱ የተሰሩት ከድንጋይ ፣ ከእንጨትና ከኖራ ሲሆን የጥንት ኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ረቂቅነትን ያንጸባርቃሉ፡፡ ይህን አገራችን የራሷ ግብረ ህንጻ አሰራር እንደነበራት በዓለም የመሰከረውን ግብረ ህንጻ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /UNESCO/ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 1979 በዓለም ቅርስነት መዘግቦታል፡፡





 

Gondar's castle towards one of the entrance gates.

 
ፋሲል ግቢ ወይንም ነገሥታት ግቢ በጎንደር ከተማ የሚገኝ የምሽጎችና የቤተመንግስታት ግምቦች ስብስብ ነው። ግቢው የተመሰረተው በ1628ዓ.ም. በዓፄ ፋሲለደስ ነበር። ማቀባበያ የሚሰኘው የግቢው አጥር 900ሜትር ርዝመት ሲኖረው በውስጡ 70፣000 ስኩየር ሜትር የመሬት ይዞታ ያካልላል። አጼ ፋሲለደስ የመጀመሪያውንና ታላቁን ግንብ ያሰሩ እንጂ፣ ከርሳቸው በኋላ የተነሱት ነገሥታትም ለ220 ዓመታት የየራሳቸውን ህንጻ በመስራት ቦታው በቅርስ እንዲዳብር አድርገዋል። በግቢው የመጨረሻውን ህንጻ ያሰራችው ንግሥት ብርሃን ሞገስ ነበርች። ግቢው ገናና በነበረበት ዘመን በሽወች የሚቆጠሩ ቤቶችና ሱቆችን በውስጡ ያቅፍ ነበር። በጥንቱ ዘመን የአስተዳደር ስርዓት ተቀርጾለት በጥንቃቄ የሚመራ ነበር። ስርዓቱም ስርዓተ መንግስት በመባል ሲታወቅ በመጽሃፍ መልኩ በግዕዝና በድሮው አማርኛ የተመዘገበ ነበር።
The grand Fasilides Castle in the Royal Enclosure at Gondar. Up till the 17th century, the rulers of Ethiopia generally did not have a permanent capital but moved around their kingdom with their entourage in fortified encampments. Emperor Fasilides broke with tradition and decided to make Gondar his capital around 1635.


The castle is set in beautiful grounds and the cool weather at 2,150 m (7,000 ft) makes for a pleasant visit.


ታሪክ ፀሃፊው ተክለፃድቅ መኩሪያ ስለ ንጉስ ፋሲል ቤተመንግስት አገነባብ ሲገልፁ አፄ ፋሲል ቤተ እስራኤሎችንና ሕንዶችን እንዳስተባበሩ ያወሳሉ፡፡ ፀሃፊው “የኢትዮጵያ አንድነት ከአፄ ልብነድንግል እስከ አፄ ቴዎድሮስ” በተሰኘ የታሪክ መፅሃፋቸው እንዳሰፈሩት፤ “ግንበኞች ሰብስበው (ፖርቱጊዞች አሉበት የሚሉ አሉ)፤ በጐንደር ከተማ እስከዛሬ የፋሲል ግንብ እየተባለ የሚታየውን ቤተመንግስት አሠሩ፡፡ ያሰራሩንም አኳኋን ከሌሎቹም እየተማከሩ ዓይነቱን የሰጡ ራሳቸው ናቸው ይባላል፡፡ ቤተመንግስቱም ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ዙርያውን ሰፊ ግንብ አሰሩ፤ በዙሪያውም አብያተክርስትያናት አሳነፁ፡፡ በዚህም ቤተመንግስት የንጉሡ ለብቻ የጳጳሱ ለብቻ ግብር ማብሊያውና ችሎት ማስቻያውም እየተለየ በየክፍሉ ስለተሰራ በጣም አምሮ ነበር፡፡ ይኸውም ያን ጊዜ አፄ ፋሲል ያሰሩት ቤተመንግስት እላይ እንዳልነው “የፋሲል ግንብ” እየተባለ ታሪካዊ የሆነ ምልክቱ ስማቸውን እያስጠራ እስከ ዛሬ ይታያል፡፡” 

The castle is surrounded by the modern city but it's future has been protected as it was recognized as a UNESCO World Heritage site in 1979.


Grand arches leading to grand empty halls. All the rooms of the castle are open to walk through.


The architecture has influences from the Portuguese, Arabs and Indians, indicating the peoples that traded with Ethiopia around the time of Fasilides.


Cages for lions that Fasilides kept to project his power.

ፋሲል መዋኛ በጎንደር ከተማ ከፋሲል ግቢ 2 ኪሎሜተር በስተ ሰሜን ምዕራብ ርቆ የሚገኝ፣ በአጼ ፋሲለደስ ዘመን ተሰረቶ የነበረው የመዋኛ ስፍራ ነው (በአንዳንዶች ዘንድ በቀዳማዊ ኢያሱ ዘመን እንደተሰራ ይጠቀሳል)። በመዋኛ ስፍራው መካከል ላይ ያለው ባለ ሁለት ፎቅ ቤት የአጼ ፋሲል መኖሪያ እንደነበር ይገመታል። በአሁኑ ዘመን፣ ለጥምቀት በዓል የሚያገለግል ሲሆን ውሃ በምድር ውስጥ በተቆፈረ ቦይ ከቀሃ ወንዝ ያገኛል። በድሮ ጊዜ በአየር በተነፋ አቅማዳ እየተንሳፈፉ ሰዎች ይዝናኑ እንደንበርና ሁልጊዜም በውሃ የተመላ እንደነበር ይነገራል። ከአጠገቡ፣ በስተምስራቅ፣ የአጼ ፋሲለደስ ፈረስ የነበረው የዞብል መቃብር ይገኛል።.                                                                                                                                                                                                                                                                                         ፋሲል መዋኛ

 

ወደ ግቢው ስዘልቅ ደስታዬ ወደር አልነበረውም። በታሪክ የማውቀውንና በህይወቴ ላየው የምጓጓለትን ታላቅ የእምነት ስፍራ በማየቴ በእውነት ሃሴትን አደረኩ። እጅግም ተደነቅኩ።
ኢትዮጵያ በየዘመኑ የነበራትን ስልጣኔ የሚዘክሩ ፤ የሕዝቦቿንም እምነት ለትውልድ የሚያስተላልፉ በርካታ የታሪክ ማስረጃዎች አሏት። አሁን ያለሁበት ቦታም ከብርቅዬ የእምነት መዘክሮች ውስጥ አንዱ ነው።
ርዕሰ አድባራት ወ ገዳማት አክሱም ፅዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን የዘመነ – አክሱም ቁንጮ የእምነት ቅርስ ናት። ይህ የደብረ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የጎንደር ዘመን አሻራ ጉልላት ሆኖ ታሪክን ይዘክራል።
እኔም ከዚህ ቀደም በስራ አጋጣሚ አክሱም ፅዮንን ተሳልሜያለሁ። አሁን ደግሞ ደብረ ብርሃን ስላሴን ለማየት ታደልኩ። ለዚህ ነው እንግዲህ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ስገባ ውስጤ ሃሴትን ያደረገው።
እኔና የሬድዮ ፋና ጋዜጠኛ ከሾፌሩ ከግርማይ ጋር ሆነን ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ያቀናነው ጀንበር ዘቅዘቅ ስትል ነበር – ሰዓቱን በእርግጠኝነት ባላስታውስም 11 ሰዓት ገደማ ይሆናል። በድንጋይ ካብ የተሠራውን አፀድ - ዘልቀን ስንገባ ቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት ይታያል። በስፍራው ለሚመሰገነው አምላክ የስግደት ሰላምታ አቅርበን ወደ ግቢው ዘለቅን።
በግቢው ውስጥ ያሉት እድሜ ጠገብ ዛፎች ለቤተ ክርስቲያኑ ተጨማሪ ግርማ ሞገስ ሆነውታል። እጅግ የሚማርከው ለምለም መስክ ደግሞ ሌላ የአይን ምግብ ። ፀሐይዋ ውሎዋን አጠናቅቃ ወደ ማደሪያዋ ልታቀና እየተጣደፈች ቢሆንም ጨረሮቿ ግን በዛፎቹ ቅርንጫፎች ሰንጥቀው እያለፉ ብርሃናቸውን በቤተ- ክርስቲያኑ ጣሪያና ገድግዳ ላይ አሳርፈዋል፡፡ ዛፎቹ በነፋስ ሲወዛወዙ በቤተ ክርስቲያኑ ላይ ከሚታየው የብርሃን ትዕይንት ጋር ተዳምሮ ልብን ይማርካል።
በአፀዱ በር ግራና ቀኝ ተቀምጠው ስለቀደሙት ቅዱሳን መንፈሳዊ ህይወት ሲጨዋወቱ ከነበሩት ሁለት ሰዎች ድምፅ ውጪ የሰው ድምፅ አይሰማም። ከየዛፎቹ ላይ የሚሰማው የአእዋፋት ህብረ – ዝማሬ ደግሞ ፍፁም የሆነ የደስታ እርካታን ይሰጣል።
የቤተ- ክርስቲያኑ በር ተከፍቷል። «ለአገልግሎት ተከፍቶ ይሆን ?» ስል አሰብኩ። እየተሳለምን ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ተመለከትን። ሰዎች አሉ። የውጭ አገር ጐብኚዎች ናቸው። አስጎብኚው በረዥም እንጨት ወደ ጣሪያና ግድግዳው እያመላከተ ያብራራል፤ ጎብኝዎችም በአንክሮ ይከታተሉታል።
እኛም በቤተ-ክርስቲያኑ ጥቂት ቆይታ አደረግን። ስለ ደብረ ብርሐን ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ከብዙ በጥቂቱ አወቅን።
ይህ ቤተ – ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ - ክርስቲያን ታሪክ ከፍተኛ ስፍራ ከሚሠጣቸው የእምነት ቦታዎች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህም የተነሳ ጐንደርን የረገጠ ጎብኚ የፋሲል አንባን እንደሚያይ ሁሉ ደብረ- ብርሃን ስላሴንም መዳረሻው ያደርጋል።
የደብረ – ብርሃን ስላሴ ቤተ -ክርስቲያን ከፋሲል ግቢ ሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ በሁለት ኪሎ ሜትር ላይ ይገኛል- እዚያው ጎንደር ከተማ ውስጥ ማለት ነው።
ቤተክርስቲያኑን ያሳነፁት ከጎንደር ዘመን ነገሥታት አንዱ የነበሩት አድያም ሰገድ እያሱ (ከ1682-1706ዓ.ም የነገሱ) ናቸው። አድያም ሰገድ ቤተክርስቲያኑን ያሠሩት በፋሲል አምባ ቤተመንግሥታቸውን ባስገነቡበት የግንባታ ቁሳቁስ – በድንጋይ፣ በኖራና በእንጨት ነው።
በታሪክ እንደሚነገረው በሸዋ በዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ ንግሥና ( ከ1434- 1468 ዓ. ም ) በሸዋው ደብረ ብርሃን ውስጥ ብርሃን ከሰማይ በመውረዱ ቤተክርስቲያኑ ደብረ ብርሃን- የብርሃን ተራራ ተባለ።
ከ200 ዓመታት በኋላ ደግሞ አድያም ሰገድ እያሱ ያሠሩት የጎንደር ሥላሴ ቤተክርስቲያንም ደብረ ብርሃን የሚል መጠሪያ ተሰጠው፡፡«ደብረ ብርሃን» የሚለውንና የሸዋው ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን የሚጠራበትን የኖረውን ስያሜ የጎንደሩ በማግኘቱም ለሸዋው ደብረ ብርሃን ሥላሴ በየዓመቱ ግብር – ስጦታ ያበረክት እንደነበር ከአንድ ጽሑፍ ላይ ተመልክቻለሁ።
ደብረብርሃን ሥላሴ በጎንደር ዘመን ከተገነቡ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያኔ እንደተገነባ ሆኖ ዛሬ ላይ የደረሰ ብቸኛው የእምነት ቦታ ነው። በታሪክ እንደተመዘገበው የጎንደር ማዕከላዊ መንግሥት ተዳክሞ፤ የመሳፍንት ዘመን እንደመጣ መሐዲስቶች ጎንደርን መዝብረዋታል፤ ክፉኛም አድቅቀዋታል።
ታዲያ በዚያን ወቅት ወራሪዎቹ በጎንደር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ አቃጠሉ። ቅርሶችንም አወደሙ። ይሁንና ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያንን ብቻ ማቃጠል ሳይቻላቸው ቀረ። የዚህ ምክንያቱ ደግሞ መሐዲስቶቹ ቤተክርስቲያኑን ሊያቃጥሉ ወደ ሥፍራው እንደደረሱ የንብ መንጋ ግቢውን ሞልቶት፤ ከቤተክርስቲያኑ በር ፊት ለፊትም ሊቀመላዕክት ቅዱስ ሚካኤል የእሳት ሰይፍ ይዞ በማየታቸው ሳያቃጥሉት ተመልሰዋል የሚል አፈ ታሪክ ይነገራል።
ቤተክርስቲያኑ ከዚያ የጥፋት ዘመን አልፎ ታዲያ ታሪክን እየዘከረ ይገኛል። ዕድሜ ጠገብ ቢሆንም የያኔውን የሕንፃ ኪን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የሬክታንግል ዓይነት ቅርጽ ያለው ሲሆን በኖህ መርከብ አምሳያ እንደተሠራም ይነገራል።
በጌጠኛ አሠራር የተዋቡት እና ለዘመን መፈራረቅ እጅ ያልሰጡት በርና መስኮቶች ያስደምማሉ። ከውበታቸው የጠንካሬያቸው ፤ ከጥንካሬያቸው ስፋትና ቁመታቸው ያስደንቃል።
የቤተክርስቲያኑ ውስጥም እንዲሁ እጅጉን ያማረ ነው- ጣሪያና ግድግዳው በዚያ ዘመን በተሳሉ ሥዕሎች ያሸበረቀ ነው። የቅድስትሥላሴን ጨምሮ ክርስቶስ ኢየሱስ በምድር ላይ የነበረውን ቆይታ የሚያሳዩ የቅድስት ድንግል ማርያምን፣ የፃድቃንንና የሰማዕታትን መንፈሳዊ ሕይወት የሚያሳዩ ሥዕሎች በግድግዳው ላይ ይታያሉ።
በፊት ለፊት የሚታየው የኢየሱስ የሥነ ስቅለት ምስልና በጣሪያው ላይ የሚታዩት በመቶዎች የሚቆጠሩ የመላዕክት ምስሎችም የዘመናት የኪነ ጥበብ አሻራ ሆነው እስከዛሬ ዘልቀዋል።ቤተክርስቲያኑ በአሁኑ ወቅት መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጠ ነው። ይሁንና እድሜው በገፋ ቁጥር አሉታዊ ተጽዕኖ ያርፍበታልና ቅርጽነቱ ተጠብቆ እንዲቆይ የሚያስችሉ አማራጮች ቢታዩ መልካም ነው እላለሁ።
ይህ የእምነት አምባ በእውነት ያስደንቃል። የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ቅርስ ብቻ ሳይሆን የመላ የኢትዮጵያውያን የታሪክ ሐውልትም ሆኖ የቱሪስት መዳረሻ ሆኗል። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንትን የሚያፈራ የትምህርት ማዕከልም ነው። ጊዜ አጥሮን ሳንጎበኘው ቀረን እንጂ በዙሪያው እጅግ በርካታ የአብነት ሊቃውንት እና ደቀ መዛሙርት እንዳሉም ተነግሮናል።
ሊለዩት የሚከብደውን ይህንኑ አስደናቂ የታሪክ እና የእምነት ቅርስ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ልንሰናበት ነው፡፡ በቤተክርስቲያኑ ጥንታዊነት፤ በቅርሶቹም ዕፁብ ድንቅነት ፤በግቢው ግርማ ሞገስና ድባብ ተደንቀን፤ ለአዕምሯችን ጣፋጭና አይረሴ ትውስታን ሰንቀን ግቢውን ተሰናበትን።
እናንተም እንደ እኔ ዕድሉን አግኝታችሁ የታሪክ አምባ የሆነችውን ጎንደርን ወዲያውም ይህንኑ አስደናቂ የእምነት፤ የጥበብና የቅርስ አምባ እንድትጎበኙ ነው የምመኝላችሁ። https://www.facebook.com/tarikuasefa


 



 


Looking up at the bamboo roof structure at Debre Berhan Selassie Church.


Outside the walls of the church compound lies an old cemetery overgrown with vegetation.


An ancient grave marker outside the walls of Debre Berhan Selassie Church.


After the cultural tour, Doug took me for a nature walk outside town that he discovered recently.


Walking along a path in the valleys surrounding Gondar.


A path forcing its way across this stone wall, leading to...



Walking back into town and passing this Walia Ibex statue. It's endemic to Ethiopia and particularly the Simien Mountains, where I was headed next.


On my second and last night at Tarara Hotel, a room opened up and they upgraded me from camping in the garden. I wanted to make an early start the next day and didn't want to have wet camping gear to pack up as the rainy season brought nightly rains.
I enjoyed my short visit to Gondar and was happy to have met some other travelers who showed me some off-the-beaten path sights around Gondar. I got my cultural fix and next up was an immersion in nature.

No comments:

Post a Comment