Monday, May 14, 2012

የእሷ ፍቅር



ተዝቆ ተዝቆ የማያልቅ
ተፍቆ ተፍቆ የማይለቅ
ተጨምቆ ተጨምቆ የማይደርቅ
የእሷ ፍቅር
ከማር በላይ ማር
ድንቅ ናት ድንቅ
የሩቅ መንገድ ስንቅ
ብርቅ ናት ብርቅ
ከወርቅ በላይ ወርቅ
ታስቀይም ይሆናል
በሆነ ምክንያት
እሷም ትቅየም ይሆናል
በሆነ ምክንያት
ሆኖም ዞሮ ዞሮ
እምዬ ናት
እናት
Endless
Boundless
Love is hers
Sweeter than sweet
The most delicate Sometimes
she might disappoint
Or
She might get disappointed
But
She is always dear mother
And
That remains unchanged

www.facebook.com/tarikuasefa

Friday, May 11, 2012

ቱሪዝም

www.facebook.com/tarikuasefaየድንቆች ምድር ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ቀልብ መሳብ የሚችሉ በርካታ ሀብቶችን ከታደሉ ጥቂት የዓለማችን ሀገሮች አንዱዋ ነች፡፡ ኢትዮጵያ የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤትም ነች፡፡ የቀደምት ስልጣኔዋ አሻራ የሆኑ ብዙ ባህላዊ ታሪካዊና የቱሪስት መስህብ ሀብቶች አሏት፡፡

ከዚህ ሌላ ኢትዮጵያ ከ80 በላይ የሆኑ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሰላምና በመቻቻል የሚኖሩባት ሃገር ናት፡፡ በዚህም የብሄረሰቦችና ቋንቋዎች ሙዚየም ለመባል በቅታለች፡፡ ሃገራችንን በአለም ላይ ታዋቂ ያደረጋት ሌላው ገጽታ ደግሞ የተለያዩ እምነቶች ተከታይ የሆኑ ህዝቦች በመተሳሰብ በጋራ የሚኖሩባት ሃገር መሆኗ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም በተለየ የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር አላት፡፡

ከዘመን አቆጣጠሩ ጋር ተያይዘው በህዝቦችዋ የሚከበሩት የሃይማኖት በዓላት /Festivals/ በርካታ ቱሪስቶች ወደ ሃገራችን እንዲጎርፉ የማድረግ አቅም አላቸው ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ በእንግዳ ተቀባይነቷ፣ በሰው ዘር መገኛነቷ፣ በነጻነት ተምሳሌትነቷ ትታወቃለች፡፡

ለመሆኑ የኢትዮጵያን የቱሪሰት መስህብ ሃብቶች በአግባቡ ያውቃሉ? ጥቂቶቹን እናስተዋውቅዎ፡፡ ሃገራችን ካሏት ድንቅ የቱሪሰት መስህብ ሃብቶች ውስጥ ዘጠኙ በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ የባሀልና ትምህርት ድርጅት /UNESCO/ በዓለም ቅርስነት ተመዝግበዋል፡፡

በዩኔስኮ በአለም ቅርስነት የተመዘገቡ ዘጠኙ የኢትዮጵያ ቅርሶች

1.የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን

በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ከቆቦ ከተማ 78 ኪ.ሜ ገባ ብላ የምትገኘው የላሊበላ ከተማ በጥንት ዘመን ሮሃ ተብላ ትጠራ ነበር፡፡ ላሊበላ የሚለውን ስም ያገኘችው አስራ አንዱን ውቅር አብያተ ክርስቲያን ከአንድ ወጥ ድንጋይ አስፈልፍለዋል ተብለው ከሚነገርላቸው ከዛጉዌ ነገስታት አንዱ ከሆኑት ከአጼ ላሊበላ ነው፡፡

በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ተፈልፍለው እንደታነጹ የሚነገርላቸው እነኝህ 11 አብያተ ክርስቲያን በአስደናቂነታቸው ወደር ያልተገኘላቸው ናቸው፡፡ በርካታ ተጓዞችና የጉዞ ጸሀፍት የላሊበላን አብያተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ዋና የቱሪስት መስህብ ሃብት “prime tourist attraction of Ethiopia” ብለው ይገልጹአቸዋል፡፡ ይህ ድንቅ የአባቶች ጥበብ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 8/1978 በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት ማህደር ውስጥ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ የመጀመሪያው የአገራችን ቅርስ ነው፡፡

2. የጎንደር አብያተ መንግስት ግብረ ህንጻ

የኢትዮጵያ ጥንታዊ ከተሞች ታሪክ ሲወሳ የጎንደር ስም ሳይጠቀስ አይታለፍም፡፡ የጎንደር ነገስታት ግብረ ህንጻዎች በአማራ ክልል ከአዲስ አበባ ሰሜን ምዕራብ 738 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ከተማ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው አጋማሽ በአጼ ፋሲለደስ ዘመን መንግስት እንደተቆረቆረች የሚነገርላት ጎንደር ከሌሎች ቀደምት ከተሞች ለየት የሚያደርጋት ለረጅም ጊዜ በመናገሻ ከተማነት ማገልገሏ ነው፡፡ በታሪክና በባሀል ነጸብራቅነቷም ትታወቃለች፡፡ የጎንደር ከተማ ዋነኛ የቱሪስት መስህብ ሃብቶች የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ነገስታት ያሰሯቸው አብያተ መንግስትና አብያተ ክርስቲያን ናቸው፡፡ አብያተ መንግስቱ በከተማ መሃል በሚገኘው ከፍተኛ ስፍራ ላይ ከአጼ ፋሲል ግቢ ቀደም ሲል 12 በሮች እንደነበሩት ይነገራል፡፡ አሁን ያለው የመግቢያ በር ከጥንቶቹ በሮች አንዱ ሳይሆን በጣሊያን ጊዜ የተሰራ ነው፡፡ አብያተ መንግስቱ የተሰሩት ከድንጋይ ፣ ከእንጨትና ከኖራ ሲሆን የጥንት ኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ረቂቅነትን ያንጸባርቃሉ፡፡ ይህን አገራችን የራሷ ግብረ ህንጻ አሰራር እንደነበራት በዓለም የመሰከረውን ግብረ ህንጻ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /UNESCO/ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 1979 በዓለም ቅርስነት መዘግቦታል፡፡

3. የአክሱም ሐውልቶች የአካባቢው አርኪኦሎጂያዊ ሥፍራ

ከአዲስ አበባ ከ1000 ኪ.ሜ ርቃ በትግራይ ብሄራዊ ክልል የምትገኘው የአክሱም ከተማ < የኢትዮጵያ የጥንት ዘመን ከተማ> (Ethiopia’s most ancient city) ትባላለች፡፡

በ3ኛው ክፍለ ዘመን በወታደራዊ ሃይልና በንግድ እንቅስቃሴያቸው የታወቁት 4 ትልልቅ ግብአቶች ባቢሎን ፣ ሮማ ፣ ግብጽና አክሱም እንደነበሩ የታሪክ መጽሐፍት ያስረዳሉ፡፡ አክሱም ጥንታዊ ቀርሶች ፣ አስደናቂ ሃውልቶች ፣ ቤተክርስቲያኖች፣ የነገስታት መቃብሮችና የቤተ መንግስት ፍርስራሾች የሚገኙባት በቱሪስት መስህብ ዝነኛ የሆነች ከተማ ነች፡፡ ጽላተ ሙሴ አርፎባታል ተብሎ የምትገመተው የአክሱም ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን የምትገኘውም በዚህች ጥንታዊና ታሪካዊ ከተማ ውስጥ ነው፡፡

የአክሱምን ሃውልቶች የተመለከተ ሁሉ የተሰሩበት ዘመን ወደ ኋላ በመቃኘት እነዚያ ግዙፍ ድንጋዮች በዚያ ዘመን እንዴት ሊቆሙ እንደቻሉ መደነቁ የማይቀር ነው፡፡

በአክሱምና በአካባቢዋ ካንድ ወጥ ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩ ከሃምሳ በላይ ሐውልቶችና የሰው ልጅ ጥንታዊ የእጅ ጥበብ ውጤቶችን በተባበሩተ መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 1980 በዓለም ቅርስነት መዘግቧቸዋል፡፡ ከአክሱም ሐውልቶች መካከል አንዱ የሆነውና 24.6 ሜትር ርዝመት ያለው እ.አ.አ በ1937 ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረች ጊዜ በፋሽስት ወታደሮቿ ተዘርፎ ወደ ሮም ተወስዶ ነበር፡፡ ይህ ሐውልት ለ68 ዓመታት በሮም አደባበይ ተተክሎ ከቆየ በኃላ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት በሚያዝያ ወር 1997 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል፡፡ ሐውልቱ በሶስት ቦታዎች ተከፍሎ በግዙፍ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን በሶስት ጊዜ ምልልስ የመጣ ሲሆን የመልሶ ተከላ ስራው ሲነከናወን ቆይቶ ነሃሴ 29/2000 ተመርቋል፡፡

4.ሐረር ጀጎል ግንብ

ጥንታዊቷ የሐረር ከተማ በምስራቅ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ 525 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ከ7ኛው አስከ 9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደተቆረቆረች የሚነገርላት የሐረር ከተማ አምስት በሮች ባሉትና ጀጎል ተብሎ በሚጠራው ዝነኛ አጥር /ግንብ/ የተከበበች ናት፡፡ ግንቡ ከ13ኛው እስከ 16ኛው መቶ ክ/ዘመን እንደተሰራ የሚነገር ሲሆን የተሰራበት ዋና አላማም ወራሪዎችን ለመከላከል እንደሆነ ይነገራል፡፡

ይህ ታሪካዊ ግንብ ለጎብኚዎች እንደ መስህብ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ሐረር ስትቆረቆር ተሰራ ተብሎ ከሚታመነው ጥንታዊ የሼክ አባድር መስጊድ ሌላ ስድስትና ሰባት መቶ አመት እድሜ ያላቸው ጥንታዊ ቤቶች ፣ የአቡ ሰኢድ አሊ መቃብር ቦታ ፣ በጥንታዊ ሰዎች የተሳሉ የዋሻ ውስጥ ስዕሎች አሉ፡፡

ከዚህ ሌላ ሐረር አንጋፋ የንግድ መናኸሪያ እና የእስልምና ትምህርት ማዕከል እንደነበረች ከታሪክ እንረዳለን፡፡ በከተማዋ ውስጥ ከ90 ያላነሱ መስጊዶች ያሉ ሲሆን 4ኛው የእስልምና ሃይማኖት ቅዱስ ከተማ ተብላ ትጠራለች፡፡ የከተማዋ መንገዶች ጠባብነት ፣ የቤት አሰራራቸው ቅርጽ ልዩ መሆን ፣ ጅብን የመመገብ ባህል ፣ ሴቶቻቸው የሚለብሷቸው ደማቅ ቀሚሶች፣ ልዩ ልዩ የዕደ ጥበብ ስራዎቻቸው ፣ ሐረርን ከሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የተለየች የቱሪስት መዳረሻ ያደርጓታል፡፡

ሐረር ከምስራቅ አፍሪካ ጥንታዊ ከተሞች አንዷ መሆኗን በማመን የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት እ.ኤ.አ በ2006 በዓለም ቅርስነት መዝግቧታል ፡፡

5. የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ አንጋፋ ብሄራዊ ፓርኮች አንዱ የሆነው የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የሚገኘው በአማራ ክልል ሰሜን ጎደር ዞን ከደባርቅ ከተማ 32 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ ፓርኩ ከባህር ወለል በላይ ከ1900-3926 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ ከፓርኩ ተራሮች ጋር ተያይዞ የሚገኘው በከፍታው ከሀገራችን አንደኛ ከአፍሪካ ደግሞ 4ኛ የሆነው ራስ ዳሽን ተራራ ከፓርኩ የማረፊያ ሰፈር በሁለት ቀን የእግር ጉዞ ላይ ይገኛል፡፡ የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ውስብስብ የተፈጥሮ ትንግርት የሚታይበት ስፍራ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ከሚገኙት ሰላሳ አንድ ጡት አጥቢ የዱር እንስሳት ሰባቱ ፣ ከአስራ ስድስት አእዋፋት ደግሞ አስራ ሶስቱ የሚገኙት በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ ነው፡፡ ዋልያ፣ የሰሜን ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮ የፓርኩ ልዩ መታወቂያዎች ናቸው፡፡ ሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት እ.ኤ.አ በ1978 በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡

6. የታችኛው ኦሞ ሸለቆ የቅርስ ሥፍራ

የታችኛው ኦሞ ሸለቆ የቅርስ ሥፍራ በደቡብ ብሄር ብህረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በደቡብ ኦሞ ዞን መስተዳድር ውስጥ ይገኛል፡፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቱርካና ሐይቅ አካባቢ የሚገኘው የታችኛው ኦሞ ሸለቆ በሰው ልጅ አመጣጥና ቅድመ ታሪክ ጥናት ከፍተኛ ሥፍራ የሚሰጠው ቦታ ነው፡፡

ከ2.4 ሚሊዮን አመት በላይ እድሜ ያላቸው ጥንታዊ ቁሳቁሶችና የሰው ዘር ቅሪተ አካሎች የተገኙበት ይህ አካባቢ የተለያዩ ጥንታዊ ባህላቸውንና አኗኗራቸውን የሚከተሉ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚኖሩባት በመሆኑ አንትሮሎጂስቶች በብዛት የሚጎርፉበት አካባቢ ነው፡፡ እጅግ በጣም በርካታ ባህላዊ ትውፊቶች በውስን አካባቢ የሚገኙበት መሆኑ የታችኛውን የኦሞ ሸለቆ በዓለም ልዩ ሥፍራ ያደርገዋል፡፡ ይኸው ሥፍራ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስና የባሀል ድርጅት እ.ኤ.አበሴፕቴምበር 1980 በአለም ቅርስነት ተመዘግቧል፡፡

7.የጥያ ትክል ድንጋዮች

የጥያ ትክል ድንጋዮች በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን ሶዶ ውስጥ ከመልካ ቁንጥሬ 40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛሉ፡፡

ትክል ድንጋዮችን ለቀብር ቦታ ምልክትነት በመጠቀም ከቀብር ሰርዓት መጀመር ጋር አብሮ ያደገ ባሀል ነው፡፡

የትክል ድንጋዮች አይነት የተለያየ ሲሆን ከአንድ ሜትር ቁመት በታች ካላቸው አንስቶ እንደ አክሱም ሐውልቶች በትክክል ተቀርጸው የቆሙ ረጃጅም ግዙፍ ትክል ድንጋዮች ድረስ አሉ፡፡

ሶዶና አካባቢው ከአምስት የማያንሱ የትክል ድንጋይ አይነቶች የሚገኙ ሲሆን ፣ ከነኝህ መካከል ባለ ሰው ቅርጽ /anthropomorphic steale/፣ ምስሎች የተቀረጹባቸው ድንጋዮችና/Figurative steale/ የወንድ ብልት ቅርጽ ያላቸው /Sword steale/ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የጥያ መካነ ቅርስ የአለም ህዝቦች የጋራ እሴት ተደርጎ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስና የባሀል ድርጅት እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 5/1980 በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው ከዚህ ታሪካዊ ፋይዳው የተነሳ ነው፡፡

8. የታችኛው አዋሽ ፓሊዮአንትሮፖሎጂና ቅድመ ታሪክ ሥፍራ

በአፋር ብህራዊ ክልላዊ መንግስት የታችኛው አዋሽ ተፋሰስ ወስጥ የሚገኘው ሃዳር በዓለም ታዋቂና ዝነኛ የሆነች የሰው ዘር ግንድ ቅሪተ አካል ሉሲ /ድንቅነሽ/ የተገኘችበት ሥፍራ ነው፡፡

አካባቢው በአፍሪካ አህጉር በጣም ጠቃሚ የሆኑ ፖሊዮ አንትሮፖሎጂና ቅሪተ አካሎች የሚገኙበት ስለሆነ የሰው ዘር ምንጭና ባህል አጥኚ ምሁራን ቀለባቸውን ኢትዮጵያ ላይ እንዲያሳርፉ አስገድዷቸዋል ፡፡ የ3.5 ሚሊዮን ዓመት እድሜ ያላት ሉሲ/ድንቅነሽ እ.ኤ.አ በ1974 መገኘት የሰው ልጅ ቆሞ መሄድ እንደጀመረ ፍንጭ የሚሰጥ እንደሆነ ሳይንቲስቶች ይናገራሉ ፡፡ በመሆኑም ይህንን ሥፍራ የተባበሩተ መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሀል ድርጅት እ.ኤ.አ 5/1980 በዓለም ቅርስነት መዝግቦታል፡፡

9.የኮንሶ ባህላዊ መንደሮች

የኮንሶ ባሀላዊ መልክዓምድር በደቡብ ኢትዮጵያ ኮንሶ ከፍታዎች ላይ የሚገኝ 55 ሰኩዌር ኪ.ሜ የሚሸፍን በድንጋይ የታጠሩ እርከኖችና የተመሸጉ መንደሮች ያሉበት ደረቅ ስፍራ ነው፡፡ ቅርሱ የ21 ትውልዶች /400 ዓመታት በላይ/ የኋላ ታሪክ ያለው ሲሆን ደረቅና አስቸጋሪ ከሆነ አካባቢ ጋር ተስማምቶ የመኖር ሕያው ባህላዊ ልማድ አስደናቂ ምሳሌ ነው፡፡ ቦታው የማህበረሰቡን የጋራ እሴቶች፣ ማህበራዊ ቁርኝትና የምህንድስና ዕውቀትን የሚያሳይ ነው፡፡ ሥፍራው በተባበሩተ መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሀል ድርጅት እ.ኤ.አ ጁን 27/ 2011 በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡

Gondar and its Castles/የጎንደር ከተማ ዋነኛ የቱሪስት መስህብ

www.facebook.com/tarikuasefaየጎንደር ነገስታት ግብረ ህንጻዎች በአማራ ክልል ከአዲስ አበባ ሰሜን ምዕራብ 738 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ከተማ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው አጋማሽ በአጼ ፋሲለደስ ዘመን መንግስት እንደተቆረቆረች የሚነገርላት ጎንደር ከሌሎች ቀደምት ከተሞች ለየት የሚያደርጋት ለረጅም ጊዜ በመናገሻ ከተማነት ማገልገሏ ነው፡፡ በታሪክና በባሀል ነጸብራቅነቷም ትታወቃለች፡፡ የጎንደር ከተማ ዋነኛ የቱሪስት መስህብ ሃብቶች የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ነገስታት ያሰሯቸው አብያተ መንግስትና አብያተ ክርስቲያን ናቸው፡፡ አብያተ መንግስቱ በከተማ መሃል በሚገኘው ከፍተኛ ስፍራ ላይ ከአጼ ፋሲል ግቢ ቀደም ሲል 12 በሮች እንደነበሩት ይነገራል፡፡ አሁን ያለው የመግቢያ በር ከጥንቶቹ በሮች አንዱ ሳይሆን በጣሊያን ጊዜ የተሰራ ነው፡፡ አብያተ መንግስቱ የተሰሩት ከድንጋይ ፣ ከእንጨትና ከኖራ ሲሆን የጥንት ኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ረቂቅነትን ያንጸባርቃሉ፡፡ ይህን አገራችን የራሷ ግብረ ህንጻ አሰራር እንደነበራት በዓለም የመሰከረውን ግብረ ህንጻ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /UNESCO/ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 1979 በዓለም ቅርስነት መዘግቦታል፡፡





 

Gondar's castle towards one of the entrance gates.

 
ፋሲል ግቢ ወይንም ነገሥታት ግቢ በጎንደር ከተማ የሚገኝ የምሽጎችና የቤተመንግስታት ግምቦች ስብስብ ነው። ግቢው የተመሰረተው በ1628ዓ.ም. በዓፄ ፋሲለደስ ነበር። ማቀባበያ የሚሰኘው የግቢው አጥር 900ሜትር ርዝመት ሲኖረው በውስጡ 70፣000 ስኩየር ሜትር የመሬት ይዞታ ያካልላል። አጼ ፋሲለደስ የመጀመሪያውንና ታላቁን ግንብ ያሰሩ እንጂ፣ ከርሳቸው በኋላ የተነሱት ነገሥታትም ለ220 ዓመታት የየራሳቸውን ህንጻ በመስራት ቦታው በቅርስ እንዲዳብር አድርገዋል። በግቢው የመጨረሻውን ህንጻ ያሰራችው ንግሥት ብርሃን ሞገስ ነበርች። ግቢው ገናና በነበረበት ዘመን በሽወች የሚቆጠሩ ቤቶችና ሱቆችን በውስጡ ያቅፍ ነበር። በጥንቱ ዘመን የአስተዳደር ስርዓት ተቀርጾለት በጥንቃቄ የሚመራ ነበር። ስርዓቱም ስርዓተ መንግስት በመባል ሲታወቅ በመጽሃፍ መልኩ በግዕዝና በድሮው አማርኛ የተመዘገበ ነበር።
The grand Fasilides Castle in the Royal Enclosure at Gondar. Up till the 17th century, the rulers of Ethiopia generally did not have a permanent capital but moved around their kingdom with their entourage in fortified encampments. Emperor Fasilides broke with tradition and decided to make Gondar his capital around 1635.


The castle is set in beautiful grounds and the cool weather at 2,150 m (7,000 ft) makes for a pleasant visit.


ታሪክ ፀሃፊው ተክለፃድቅ መኩሪያ ስለ ንጉስ ፋሲል ቤተመንግስት አገነባብ ሲገልፁ አፄ ፋሲል ቤተ እስራኤሎችንና ሕንዶችን እንዳስተባበሩ ያወሳሉ፡፡ ፀሃፊው “የኢትዮጵያ አንድነት ከአፄ ልብነድንግል እስከ አፄ ቴዎድሮስ” በተሰኘ የታሪክ መፅሃፋቸው እንዳሰፈሩት፤ “ግንበኞች ሰብስበው (ፖርቱጊዞች አሉበት የሚሉ አሉ)፤ በጐንደር ከተማ እስከዛሬ የፋሲል ግንብ እየተባለ የሚታየውን ቤተመንግስት አሠሩ፡፡ ያሰራሩንም አኳኋን ከሌሎቹም እየተማከሩ ዓይነቱን የሰጡ ራሳቸው ናቸው ይባላል፡፡ ቤተመንግስቱም ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ዙርያውን ሰፊ ግንብ አሰሩ፤ በዙሪያውም አብያተክርስትያናት አሳነፁ፡፡ በዚህም ቤተመንግስት የንጉሡ ለብቻ የጳጳሱ ለብቻ ግብር ማብሊያውና ችሎት ማስቻያውም እየተለየ በየክፍሉ ስለተሰራ በጣም አምሮ ነበር፡፡ ይኸውም ያን ጊዜ አፄ ፋሲል ያሰሩት ቤተመንግስት እላይ እንዳልነው “የፋሲል ግንብ” እየተባለ ታሪካዊ የሆነ ምልክቱ ስማቸውን እያስጠራ እስከ ዛሬ ይታያል፡፡” 

The castle is surrounded by the modern city but it's future has been protected as it was recognized as a UNESCO World Heritage site in 1979.


Grand arches leading to grand empty halls. All the rooms of the castle are open to walk through.


The architecture has influences from the Portuguese, Arabs and Indians, indicating the peoples that traded with Ethiopia around the time of Fasilides.


Cages for lions that Fasilides kept to project his power.

ፋሲል መዋኛ በጎንደር ከተማ ከፋሲል ግቢ 2 ኪሎሜተር በስተ ሰሜን ምዕራብ ርቆ የሚገኝ፣ በአጼ ፋሲለደስ ዘመን ተሰረቶ የነበረው የመዋኛ ስፍራ ነው (በአንዳንዶች ዘንድ በቀዳማዊ ኢያሱ ዘመን እንደተሰራ ይጠቀሳል)። በመዋኛ ስፍራው መካከል ላይ ያለው ባለ ሁለት ፎቅ ቤት የአጼ ፋሲል መኖሪያ እንደነበር ይገመታል። በአሁኑ ዘመን፣ ለጥምቀት በዓል የሚያገለግል ሲሆን ውሃ በምድር ውስጥ በተቆፈረ ቦይ ከቀሃ ወንዝ ያገኛል። በድሮ ጊዜ በአየር በተነፋ አቅማዳ እየተንሳፈፉ ሰዎች ይዝናኑ እንደንበርና ሁልጊዜም በውሃ የተመላ እንደነበር ይነገራል። ከአጠገቡ፣ በስተምስራቅ፣ የአጼ ፋሲለደስ ፈረስ የነበረው የዞብል መቃብር ይገኛል።.                                                                                                                                                                                                                                                                                         ፋሲል መዋኛ

 

ወደ ግቢው ስዘልቅ ደስታዬ ወደር አልነበረውም። በታሪክ የማውቀውንና በህይወቴ ላየው የምጓጓለትን ታላቅ የእምነት ስፍራ በማየቴ በእውነት ሃሴትን አደረኩ። እጅግም ተደነቅኩ።
ኢትዮጵያ በየዘመኑ የነበራትን ስልጣኔ የሚዘክሩ ፤ የሕዝቦቿንም እምነት ለትውልድ የሚያስተላልፉ በርካታ የታሪክ ማስረጃዎች አሏት። አሁን ያለሁበት ቦታም ከብርቅዬ የእምነት መዘክሮች ውስጥ አንዱ ነው።
ርዕሰ አድባራት ወ ገዳማት አክሱም ፅዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን የዘመነ – አክሱም ቁንጮ የእምነት ቅርስ ናት። ይህ የደብረ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የጎንደር ዘመን አሻራ ጉልላት ሆኖ ታሪክን ይዘክራል።
እኔም ከዚህ ቀደም በስራ አጋጣሚ አክሱም ፅዮንን ተሳልሜያለሁ። አሁን ደግሞ ደብረ ብርሃን ስላሴን ለማየት ታደልኩ። ለዚህ ነው እንግዲህ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ስገባ ውስጤ ሃሴትን ያደረገው።
እኔና የሬድዮ ፋና ጋዜጠኛ ከሾፌሩ ከግርማይ ጋር ሆነን ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ያቀናነው ጀንበር ዘቅዘቅ ስትል ነበር – ሰዓቱን በእርግጠኝነት ባላስታውስም 11 ሰዓት ገደማ ይሆናል። በድንጋይ ካብ የተሠራውን አፀድ - ዘልቀን ስንገባ ቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት ይታያል። በስፍራው ለሚመሰገነው አምላክ የስግደት ሰላምታ አቅርበን ወደ ግቢው ዘለቅን።
በግቢው ውስጥ ያሉት እድሜ ጠገብ ዛፎች ለቤተ ክርስቲያኑ ተጨማሪ ግርማ ሞገስ ሆነውታል። እጅግ የሚማርከው ለምለም መስክ ደግሞ ሌላ የአይን ምግብ ። ፀሐይዋ ውሎዋን አጠናቅቃ ወደ ማደሪያዋ ልታቀና እየተጣደፈች ቢሆንም ጨረሮቿ ግን በዛፎቹ ቅርንጫፎች ሰንጥቀው እያለፉ ብርሃናቸውን በቤተ- ክርስቲያኑ ጣሪያና ገድግዳ ላይ አሳርፈዋል፡፡ ዛፎቹ በነፋስ ሲወዛወዙ በቤተ ክርስቲያኑ ላይ ከሚታየው የብርሃን ትዕይንት ጋር ተዳምሮ ልብን ይማርካል።
በአፀዱ በር ግራና ቀኝ ተቀምጠው ስለቀደሙት ቅዱሳን መንፈሳዊ ህይወት ሲጨዋወቱ ከነበሩት ሁለት ሰዎች ድምፅ ውጪ የሰው ድምፅ አይሰማም። ከየዛፎቹ ላይ የሚሰማው የአእዋፋት ህብረ – ዝማሬ ደግሞ ፍፁም የሆነ የደስታ እርካታን ይሰጣል።
የቤተ- ክርስቲያኑ በር ተከፍቷል። «ለአገልግሎት ተከፍቶ ይሆን ?» ስል አሰብኩ። እየተሳለምን ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ተመለከትን። ሰዎች አሉ። የውጭ አገር ጐብኚዎች ናቸው። አስጎብኚው በረዥም እንጨት ወደ ጣሪያና ግድግዳው እያመላከተ ያብራራል፤ ጎብኝዎችም በአንክሮ ይከታተሉታል።
እኛም በቤተ-ክርስቲያኑ ጥቂት ቆይታ አደረግን። ስለ ደብረ ብርሐን ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ከብዙ በጥቂቱ አወቅን።
ይህ ቤተ – ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ - ክርስቲያን ታሪክ ከፍተኛ ስፍራ ከሚሠጣቸው የእምነት ቦታዎች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህም የተነሳ ጐንደርን የረገጠ ጎብኚ የፋሲል አንባን እንደሚያይ ሁሉ ደብረ- ብርሃን ስላሴንም መዳረሻው ያደርጋል።
የደብረ – ብርሃን ስላሴ ቤተ -ክርስቲያን ከፋሲል ግቢ ሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ በሁለት ኪሎ ሜትር ላይ ይገኛል- እዚያው ጎንደር ከተማ ውስጥ ማለት ነው።
ቤተክርስቲያኑን ያሳነፁት ከጎንደር ዘመን ነገሥታት አንዱ የነበሩት አድያም ሰገድ እያሱ (ከ1682-1706ዓ.ም የነገሱ) ናቸው። አድያም ሰገድ ቤተክርስቲያኑን ያሠሩት በፋሲል አምባ ቤተመንግሥታቸውን ባስገነቡበት የግንባታ ቁሳቁስ – በድንጋይ፣ በኖራና በእንጨት ነው።
በታሪክ እንደሚነገረው በሸዋ በዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ ንግሥና ( ከ1434- 1468 ዓ. ም ) በሸዋው ደብረ ብርሃን ውስጥ ብርሃን ከሰማይ በመውረዱ ቤተክርስቲያኑ ደብረ ብርሃን- የብርሃን ተራራ ተባለ።
ከ200 ዓመታት በኋላ ደግሞ አድያም ሰገድ እያሱ ያሠሩት የጎንደር ሥላሴ ቤተክርስቲያንም ደብረ ብርሃን የሚል መጠሪያ ተሰጠው፡፡«ደብረ ብርሃን» የሚለውንና የሸዋው ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን የሚጠራበትን የኖረውን ስያሜ የጎንደሩ በማግኘቱም ለሸዋው ደብረ ብርሃን ሥላሴ በየዓመቱ ግብር – ስጦታ ያበረክት እንደነበር ከአንድ ጽሑፍ ላይ ተመልክቻለሁ።
ደብረብርሃን ሥላሴ በጎንደር ዘመን ከተገነቡ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያኔ እንደተገነባ ሆኖ ዛሬ ላይ የደረሰ ብቸኛው የእምነት ቦታ ነው። በታሪክ እንደተመዘገበው የጎንደር ማዕከላዊ መንግሥት ተዳክሞ፤ የመሳፍንት ዘመን እንደመጣ መሐዲስቶች ጎንደርን መዝብረዋታል፤ ክፉኛም አድቅቀዋታል።
ታዲያ በዚያን ወቅት ወራሪዎቹ በጎንደር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ አቃጠሉ። ቅርሶችንም አወደሙ። ይሁንና ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያንን ብቻ ማቃጠል ሳይቻላቸው ቀረ። የዚህ ምክንያቱ ደግሞ መሐዲስቶቹ ቤተክርስቲያኑን ሊያቃጥሉ ወደ ሥፍራው እንደደረሱ የንብ መንጋ ግቢውን ሞልቶት፤ ከቤተክርስቲያኑ በር ፊት ለፊትም ሊቀመላዕክት ቅዱስ ሚካኤል የእሳት ሰይፍ ይዞ በማየታቸው ሳያቃጥሉት ተመልሰዋል የሚል አፈ ታሪክ ይነገራል።
ቤተክርስቲያኑ ከዚያ የጥፋት ዘመን አልፎ ታዲያ ታሪክን እየዘከረ ይገኛል። ዕድሜ ጠገብ ቢሆንም የያኔውን የሕንፃ ኪን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የሬክታንግል ዓይነት ቅርጽ ያለው ሲሆን በኖህ መርከብ አምሳያ እንደተሠራም ይነገራል።
በጌጠኛ አሠራር የተዋቡት እና ለዘመን መፈራረቅ እጅ ያልሰጡት በርና መስኮቶች ያስደምማሉ። ከውበታቸው የጠንካሬያቸው ፤ ከጥንካሬያቸው ስፋትና ቁመታቸው ያስደንቃል።
የቤተክርስቲያኑ ውስጥም እንዲሁ እጅጉን ያማረ ነው- ጣሪያና ግድግዳው በዚያ ዘመን በተሳሉ ሥዕሎች ያሸበረቀ ነው። የቅድስትሥላሴን ጨምሮ ክርስቶስ ኢየሱስ በምድር ላይ የነበረውን ቆይታ የሚያሳዩ የቅድስት ድንግል ማርያምን፣ የፃድቃንንና የሰማዕታትን መንፈሳዊ ሕይወት የሚያሳዩ ሥዕሎች በግድግዳው ላይ ይታያሉ።
በፊት ለፊት የሚታየው የኢየሱስ የሥነ ስቅለት ምስልና በጣሪያው ላይ የሚታዩት በመቶዎች የሚቆጠሩ የመላዕክት ምስሎችም የዘመናት የኪነ ጥበብ አሻራ ሆነው እስከዛሬ ዘልቀዋል።ቤተክርስቲያኑ በአሁኑ ወቅት መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጠ ነው። ይሁንና እድሜው በገፋ ቁጥር አሉታዊ ተጽዕኖ ያርፍበታልና ቅርጽነቱ ተጠብቆ እንዲቆይ የሚያስችሉ አማራጮች ቢታዩ መልካም ነው እላለሁ።
ይህ የእምነት አምባ በእውነት ያስደንቃል። የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ቅርስ ብቻ ሳይሆን የመላ የኢትዮጵያውያን የታሪክ ሐውልትም ሆኖ የቱሪስት መዳረሻ ሆኗል። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንትን የሚያፈራ የትምህርት ማዕከልም ነው። ጊዜ አጥሮን ሳንጎበኘው ቀረን እንጂ በዙሪያው እጅግ በርካታ የአብነት ሊቃውንት እና ደቀ መዛሙርት እንዳሉም ተነግሮናል።
ሊለዩት የሚከብደውን ይህንኑ አስደናቂ የታሪክ እና የእምነት ቅርስ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ልንሰናበት ነው፡፡ በቤተክርስቲያኑ ጥንታዊነት፤ በቅርሶቹም ዕፁብ ድንቅነት ፤በግቢው ግርማ ሞገስና ድባብ ተደንቀን፤ ለአዕምሯችን ጣፋጭና አይረሴ ትውስታን ሰንቀን ግቢውን ተሰናበትን።
እናንተም እንደ እኔ ዕድሉን አግኝታችሁ የታሪክ አምባ የሆነችውን ጎንደርን ወዲያውም ይህንኑ አስደናቂ የእምነት፤ የጥበብና የቅርስ አምባ እንድትጎበኙ ነው የምመኝላችሁ። https://www.facebook.com/tarikuasefa


 



 


Looking up at the bamboo roof structure at Debre Berhan Selassie Church.


Outside the walls of the church compound lies an old cemetery overgrown with vegetation.


An ancient grave marker outside the walls of Debre Berhan Selassie Church.


After the cultural tour, Doug took me for a nature walk outside town that he discovered recently.


Walking along a path in the valleys surrounding Gondar.


A path forcing its way across this stone wall, leading to...



Walking back into town and passing this Walia Ibex statue. It's endemic to Ethiopia and particularly the Simien Mountains, where I was headed next.


On my second and last night at Tarara Hotel, a room opened up and they upgraded me from camping in the garden. I wanted to make an early start the next day and didn't want to have wet camping gear to pack up as the rainy season brought nightly rains.
I enjoyed my short visit to Gondar and was happy to have met some other travelers who showed me some off-the-beaten path sights around Gondar. I got my cultural fix and next up was an immersion in nature.

Thursday, May 10, 2012

መራር ስነግጥሞች

www.facebook.com/tarikuasefawww.facebook.com/tarikuasefa

ባልን ቢያስተያዩት - ከሚስ ጋራ፣
እሷ አፍለኛ ሆነች - ! ሻጋታ እንጀራ፣ 
(መንግስቱ ለማ)

* * *
ይህ የናንተ ዘመን፣
ለካስ ከስሮ ኖሯል- የዘመን መናኛ፣
ያጠናፈረው ነው - የመታውመጋኛ፣
የደገመው ዳፍንት፣
ከፍ ብሎ አጋሰስ- ዝቅ ብሎጌኛ፣
(ዮሃንስ አድማሱ)
* * *
ዝናቡ ዘነበ  - ደጁ ረሰረሰ፣
ቤት ያላችሁ ግቡ  - የኛማ ፈረሰ፣ 
(የአማራ አርሶአደሮች) 

* * *
አባቶቻችን ምን አሉ?
እናቶቻችን ምን አሉ?
እረ ምንኛውን - ከቶ ምን ይላሉ?
ሁሉም ተሰብስበው - ጭቃ ያቦካሉ፣
ብቻ ማለቁ ነው - ውሃቸው ሁሉ፣ 
(ዮሃንስ አድማሱ) 
* * *
እናንት ቡችላዎችእንደምን አላችሁ?
እኔን ተከተሉኝ - አንድ ላይ ሆናችሁ፣
እሰጣችሁዋለሁኬክ ለያንዳንዳችሁ፣
እናንት ደደቦች!
አእምሮ ግን መስጠትአልችልም ይግባችሁ! 
(አሌክሳንድር ፑሽኪን) 
* * *
በክርስቶስ ፈንታ - ፈልጉ ክርታስ፣
የምንለጥፍበት  - የጊዜውን ነፍስ፣
በስላሴ ፈንታ - ፈልጉ ሰሌዳ፣
የምንደጉስበት - የጊዜውን ፍዳ፣ 
(ዮሃንስ አድማሱ)
* * *
አይንን ካበባ - ጆሮን ከሙዚቃ፣
ጣትን ከፒያኖ - ብራናን ከመቃ፣
ብእርን ከወረቀት - ብሩሽን ከሸራ፣
ምን ደግመው ቢጥሉ - መሆን ቢከጅሉ፣
ሞዛርትና ሳልዬር - ማለት ለየቅሉ፣
(አበራ ለማ) 
* * * 
ይማጅ ኒኸሻና፣
ይማጅ ኒቄና፣
ይማጅ ዩቅ አለው፣
ይማጅ ፈረዴይ፣ 
(ትርጉም)
የተሻለውን እንፈልጋለን፣
የተሻለውን ግን አናውቅም፣
የተሻለውን የምታውቅ ፈጣሪ ሆይ፣
የተሻለውን አምጣልን፣ 
( የሃረሪ ህዝብ) 
* * *
እኛ የሳልነው ጥርስ ካልጠረሰ በኛ፣
ለኛ ዘሮች ጦስ ነው - የሕይወት መጋኛ፣
ስለዚህ ሰዎቼ - እኔ እምቧ አልኳቸው፣
ምናልባት አጥንቴ - መረቅ ቢሆናቸው። 
(ዳኛቸው ወርቁ)
* * *
በዚህ ሙት ሕዝብ፣ በድክመቱ ብትልቁ፥ በፈተናው ብትበልጡ፣
በብሶቱ ብትፈይዱ፣
በመክሊቱ ብትነግዱ
ይህ ፍጹም ባድማ፣ ይህ ፍጹም ድቅድቅ ጨለማ
እሚበራ እንዳይመስላችሁ፣ በናንት የይስሙላ ቁራጭ ሻማ። 
(ደበበ ሰይፉ) 
* * *
ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!
ካልተጠነቀቅህ ካልበረታህ - ትሞታለህ፤
ኢትዮጵያ ሰውን ትከዳለች!
(የአድአ በርጋ ኦሮሞ) 
* * *
ተማምለን ነበር - በጋራ ልናርስ፣
ቃልኪዳን ነበረን - በጋራ ልናፍስ፣
ማተብ የሌለው ሰው - ሆዱን የሚወድ፣
ዘሬን ሸጦ በልቶ - አደረገኝ ጉድ፣
(ቅኔ - አንዳርጋቸው ፅጌ )

Wednesday, May 9, 2012

ወልዶ መሣም

የአብራኬ ክፋይ ፣የቅስሜ
የእኔነቴ ውርስ፣የደሜ
በምድር፣የብቻ ትርጉሜ
ማግኘት፣እንዲህ ይጥማልና፣ለስሜ
     የመልኬን ቅጂ ጥላ መሣይ
     ሁለመናዬ ሠርፆበት ሲታይ
     ገፄ በፀዳሉ ላይ
     ምስሉ ስለ እኔ ሲያወያይ
     ለካ ወልዶ ላየ ነው ዕርካታው፡፡
ማማ፣ ባባ ሲል በኮልታፋው
በእምቦቀቅላ አፉ ሚናኘው
ድክድክ ሲል ባልጠነከረው
በህፃን ገላ ጨቅላው
የጠረኑ ለዛ መዓዛው
ለካ እንዲህ ነበርና ሚያውደው ፡፡
     ወልዶ የመሣም ፍችው
     አውቆ ላጣጣመ ቃናው
     የፍስሀ ትሩፋት ፀጋው
     በመሐፀን ሣለ ለባረከው
በእግዜር ፊት ስለውሎው
የሚያሣርጉ መላዕክታት ያለውwww.facebook.com/tarikuasefa
ህፃን ፣ ወልዶ መሣም ጣዕምናው
ለካ :እንዲህ ነበርና ደስታው
ለወላጅ :የውስጥ እርካታ እሚሠጠው፡፡
የአብራኬ ክፋይ ፣የቅስሜ
የእኔነቴ ውርስ፣የደሜ
በምድር፣የብቻ ትርጉሜ
ማግኘት፣እንዲህ ይጥማልና፣ለስሜ
     የመልኬን ቅጂ ጥላ መሣይ
     ሁለመናዬ ሠርፆበት ሲታይ
     ገፄ በፀዳሉ ላይ
     ምስሉ ስለ እኔ ሲያወያይ
     ለካ ወልዶ ላየ ነው ዕርካታው፡፡
ማማ፣ ባባ ሲል በኮልታፋው
በእምቦቀቅላ አፉ ሚናኘው
ድክድክ ሲል ባልጠነከረው
በህፃን ገላ ጨቅላው
የጠረኑ ለዛ መዓዛው
ለካ እንዲህ ነበርና ሚያውደው ፡፡
     ወልዶ የመሣም ፍችው
     አውቆ ላጣጣመ ቃናው
     የፍስሀ ትሩፋት ፀጋው
     በመሐፀን ሣለ ለባረከው
በእግዜር ፊት ስለውሎው
የሚያሣርጉ መላዕክታት ያለው
ህፃን ፣ ወልዶ መሣም ጣዕምናው
ለካ :እንዲህ ነበርና ደስታው
ለወላጅ :የውስጥ እርካታ እሚሠጠው፡፡